Fana: At a Speed of Life!

15 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢንጀንደር ሄልዝ ኢትዮጵያ ለጤና ሚኒስቴር 15 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡

የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ ኢንጀንደር ሄልዝ በእናቶችና ህፃናት ጤና በተለይም በቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ላይ አበርክቶቱ የጎላ ነው ብለዋል፡፡

እንደ ሃገር መንግስት አጋር ድርጅቶችን በማስተባበር መጠነ ሰፊ ሃብቶችን በማስተባበር ህብረተሰቡ ጋር እንዲደርስ በማድረግ የኮሮና ቫይረስን የመከላከል ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንም ሚኒስትር ዲኤታው ተናግረዋል፡፡

ኢንጀንደር ሄልዝ ኢትዮጵያ በሁሉም ክልሎችና በሁለት ከተማ አስተዳደሮች ከ300 በላይ ወረዳዎች በእናቶችና ህፃናት ጤና ላይ እየሰራ ይገኛል፡፡

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ኢንጀንደር ሄልዝ ኢትዮጵያ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመሆን የተለያዩ ስራዎችን በ13 ቋንቋዎች በሚዲያ እየሰራ መሆኑን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.