የዓለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ይጀመራልየዓለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ይጀመራል
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮሎምቢያ ካሊ የሚካሄደው የዓለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ሲጀምር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ ርቀቶች ይሳተፋሉ፡፡
በዚህም መሰረት ምሽት 12: 00 ሰዓት የወንዶች 1500 ሜትር የማጣሪያ ውድድር የሚደረግ ሲሆን፥ ምሽት 12:30 ደግሞ የሴቶች 3 ሺህ ሜትር መሰናክል ማጣሪያ ውድድር ይካሄዳል፡፡
የፍፃሜ ውድድሮች ሌሊት የሚደረጉ ሲሆን ከምሽቱ 7: 00 የሴቶች 3 ሺህ ሜትር ፍፃሜ እንዲሁም ሌሊት 7: 55 የወንዶች 5 ሺህ ሜትር የፍጻሜ ውድድር ይደረጋሉ፡፡
በተመሳሳይ ምሽት 1 : 08 የሴቶች 800 ሜትር ማጣሪያ ውድድር የሚካሄድ መሆኑን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡