Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ባህር ዳር ከተማና አዳማ ከተማ ድል ቀናቸው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ባህር ዳር ከተማ እና አዳማ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል፡፡

በፕሪምየር ሊጉ የ23ኛ ሣምንት መርሐ ግብር በዛሬው እለት በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል፡፡

ቀን 9 ሰዓት ላይ በተካሄደ ጨዋታ አዳማ ከተማ ነቢል ኑሪ ባስቆጠራት ጎል ሻሸመኔ ከተማን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

በተመሳሳይ ምሽት 12 ሠዓት ላይ በተደረገ ጨዋታ ባህር ዳር ከተማ ድሬዳዋ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡

የባህር ዳር ከተማን የማሸነፊያ ጎል ሀብታሙ ታደሰ ማስቆጠሩንም የፕሪሚየር ሊጉ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.