በሙምባይ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ ማለዳ በሕንድ በተካሄደው የሙምባይ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታዎች አሸነፉ።
በሴቶች ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1ኛ እስከ 8ኛ ተከታትለው በመግባት በበላይት አጠናቀዋል፡፡
በውድድሩ አትሌት አንቺዓለም ሃይማኖት 2 ሰዓት ከ24 ደቂቃ ከ15 ሰከንድ በመግባት የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል ጭምር አሸንፋለች፡፡
አትሌት ረሂማ ቱሳ እና አትሌት ለተብርሃን ኃይላይ 2ኛ እና 3ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቀዋል፡፡
በወንዶች አትሌት ለሚ ብርሃኑ 2 ሰዓት ከ7 ደቂቃ ከ32 ሰከንድ በመግባት የቦታውን ክብረ ወሰን በማሻሻል አሸንፏል፡፡
ኬንያዊው አትሌት ፊልሞን ሮኖ 2ኛ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ኃይሉ ዘውዱ 3ኛ ደረጃን ይዘው ውድድሩን ጨርሰዋል፡፡