Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የግብጽ አቻውን 2 ለባዶ አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ ምሽት በተካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የግብፅ አቻውን 2 ለባዶ አሸንፏል፡፡

ለኢትዮጵያን ብሔራዊ ቡድን ሁለቱን ጎሎች ዳዋ ሁቴሳ በ21 ደቂቃ እና ሽመልስ በቀለ በ40ኛው ደቂቃ አስቆጥረዋል፡፡

በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የምድቡን ሁለተኛ ጨዋታ ከግብጽ አቻው ጋር አካሂዷል፡፡

ዋልያዎቹ እና ፈረኦኖቹ  በማላዊ ዋና ከተማ በሊሎንግዌ በሚገኘው ቢንጉ ብሄራዊ ስታዲያም ነው ጨዋታቸውን ያካሄዱት፡፡

በአሠልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በምድብ 4 ከግብፅ ፣ ጊኒ እና ማላዊ ጋር ተደልድሎ ውድድሩን ያካሄደ ሲሆን፥ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከማላዊ ጋር አከናውኖ ሁለት ለአንድ መረታቱ ይታወሳል።

የአፍሪካ ዋንጫ መስራች ከነበሩ ሦስት ሀገራት መካከል የሚገኙት ኢትዮጵያ እና ግብፅ የቀደመ የእግር ኳስ ተቀናቃኝ ቡድኖች ሲሆኑ፥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ገለልተኛ በሆነ ስታዲየም ዛሬ ምሽት ባካሄደው ውድድር ከግብ ብልጫ በተጨማሪ የጨዋታ ብልጫም አሳይቶ የግብፅ አቻውን ሁለት ለባዶ በማሸነፍ ታሪካዊ ውጤት አስመዝግቧል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.