Fana: At a Speed of Life!

ዛሬ ምሽትና ሌሊት ላይ በሚካሄዱ የማጣሪያና ፍፃሜ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይሳተፋሉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም ከ20 ዓመት በታች ሻምፒዮና ዛሬ ምሽትና ሌሊት ላይ በሚካሄዱ የማጣሪያና የፍፃሜ ውድድሮ ኢትዮጵያውያን አትሌቶቸቸ ይሳተፋሉ፡፡

ምሽት 12 ሰዓት ከ5 ላይ በሚካሄድ የወንዶች 800 ሜትር ማጣሪያ ውድድር÷ ኤርሚያስ ግርማ እና መርሲሞይ ካሳሁን  ኢትዮጵያን ይወክላሉ፡፡

በሌላ መርሐ ግብር ደግሞ ምሽት 1 ሰዓት ከ5 ላይ የሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር ማጣሪያ ውድድር የሚካሄድ ሲሆን÷ ብርሂት መኮንን እና ብርቄ ኃየሎም  ኢትዮጵያን ወክለው እንደሚሳተፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

እንዲሁም ሌሊት 7 ሰዓት ከ20 ላይ በሚካሄደው የሴቶች 3 ሺህ ሜትር የመሠናክል ፍጻሜ ውድድር÷ ሲምቦ ዓለማየሁ እና መሠረት የሻነህ ይሳተፋሉ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.