Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል ለመውሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላላፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ለ1497ኛው የመውሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላላፈ።

የመውሊድ በዓል በእስልምና ዕምነት ተከታዮቾ ዘንድ ተከበረ።

በዓሉን አስመልክቶ የክልሉ መንግስት ባወጣው መግለጫ፥ “የመውሊድ በዓልን ስናከብር በክልሉ ሕዝብ ላይ በተደጋጋሚ በተፈጸሙ ወረራዎች፣ ጥቃቶች፣ ጦርነትና የድርቅ ክስተቶች ምክንያት ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው ከሚገኙ ወገኖቻችን ጋር አብሮ በማክበርና ሃይማኖታዊ አስተምህሮትን በነባራዊ ሕይወታችን የመግለጥ መንፈሳዊ ኃላፊነታችንን በመወጣት መሆን ይኖርበታል” ብሏል።

የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፦

እንኳን ለ1497ኛው የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
የዓለማት ሁሉ ፈጣሪ ቃል በሆነው በታላቁ ቁርዓን ውስጥ “እኛ ለዓለማት እዝነት አድርገን እንጂ ለሌላ አልላክንህም” ሲል እንደመሰከረው አምላክ በፈጠራቸው ዓለማት ሁሉ ላይ በቸረው እዝነት መልእክተኛ አድርጎ ላላቃቸው የነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) 1497ኛ የልደት(የመውሊድ) በዓል
ለመላው የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች እንኳን በሰላም አደረሳችሁ።

መላው ሕዝበ ሙስሊም 1497ኛ የመውሊድ በዓልን ሲያከብር የታላቁ ነቢይ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ጽኑ አስተምህሮትና ለዓለማት የመላካቸው ምክንያት የሆነውን የእዝነት፣ የርህራሄ፣ የቸርነት ሰብእናን በመጎናጸፍ እና እርስ በእርስ የመደጋገፍ በጎ አኗኗሩን ይበልጥ የሚያጠናክርበት ሊሆን ይገባል፡፡

የመውሊድ በዓልን ስናከብር በተለይም በአማራ ክልል ሕዝብ ላይ በተደጋጋሚ በተፈጸሙ ወረራዎች፣ ጥቃቶች፣ ጦርነትና የድርቅ ክስተቶች ምክንያት ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው ከሚገኙ ወገኖቻችን ጋር አብሮ በማክበርና ሃይማኖታዊ አስተምህሮትን በነባራዊ ሕይወታችን የመግለጥ መንፈሳዊ ኃላፊነታችንን በመወጣት መሆን ይኖርበታል።

መልካም የመውሊድ በዓል! ዒድ ሙባረክ !!

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
መስከረም 27ቀን 2015 ዓ.ም.
ባሕር ዳር

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.