Fana: At a Speed of Life!

በብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ላይ ለመታደም የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ ከንቲባዎችና የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ሐዋሳ እየገቡ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በሲዳማ ክልል አስተናጋጅነት ነገ በሚከበረው 17ኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ላይ ለመታደም የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች ፣ ከንቲባዎችና የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ሐዋሳ ከተማ መግባት ጀምረዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህን ጨምሮ የፓርቲው ሥራ አሥፈጻሚ ኮሚቴ አባላትም ሐዋሳ መግባታቸው ነው የተገለጸው፡፡

እንግዶቹ ሐዋሳ ከተማ ሲደርሱ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ እና ሌሎች የክልሉ ባለሥልጣናት አቀባበል እንዳደረጉላቸው ኢዜአ ዘግቧል።

ነገ በሐዋሳ ከተማ ለሚከበረው 17ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ዝግጅት መጠናቀቁን የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞ መግለጻቸው ይታወሳል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.