Fana: At a Speed of Life!

የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዳማ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ 1ኛ መደበኛ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ተጠናቋል፡፡
 
ጉባዔው “ለኢትዮጵያና አፍሪካዊ ብልጽግና የሚተጋ ወጣት” በሚል መሪ ቃል ነው ከታህሳስ 21 እስከ 25ቀን 2015 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ሲካሄድ የቆየው፡፡
 
ጉባኤው ከሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች የሊጉ አባል የሆኑ ወጣቶች በፍትሃዊ ውክልና የተሳተፉበት እንደነበር ተገልጿል፡፡
 
ጉባኤው በዛሬው ዕለት የአቋም መግለጫ በማውጣት መጠናቀቁንም ከብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.