Fana: At a Speed of Life!

የአደጋ ስጋት ቅነሳና አካታች የኢኮኖሚ ዕሴት ማሻሻያ ፕሮጀክትን ወደ ሥራ ለማስገባት ምክክር ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአደጋ ስጋት ቅነሳና አካታች የኢኮኖሚ ዕሴት ማሻሻያ ፕሮጀክትን ወደ ሥራ ለማስገባት የግብርና ሚኒስቴር፣ አጋር የልማት ድርጅቶች እና ባለድርሻ አካላት ተወያዩ፡፡

በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ እንደገለፁት÷ የአደጋ ስጋት መቀነስንና የአርብቶ አደር የኢኮኖሚ ዕሴት ማሻሻልን ማዕከል ያደረገ ፕሮጀክት ከምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት በኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያና ጅቡቲ ተግባዊ ይደረጋል፡፡

ፕሮጀክቱ ከኢትዮጵያ የቆዳ ስፋት 60 በመቶ የሚሸፍነውን የአርብቶ አደር አካባቢዎች የሚያካትት ነው ተብሏል፡፡

የአርብቶ አደሮችን ኑሮ ለማሻሻል ለተቀረፀው አዲሱ ፕሮጀክት ትግበራ የዓለም ባንክ 124 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ማድረጉን ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አርብቶአደር ያለባቸው ክልሎች በፍጥነት ወደ ሥራ አስገብተው ፕሮጀክቱን በአግባቡ በመተግበር የአርብቶ አደሩን ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ኃላፊነት እንዳለባቸው ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.