Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ መገናኛ አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሥድሥት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡
 
ዛሬ ከምሽቱ 1:12 ሰዓት ገደማ መገናኛ አደባባይ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ እስካሁን የ6 ሰዎች ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ ተናግረዋል፡፡
 
በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸውን ተጎጂዎች በአንቡላንስ ወደ ተለያዩ ጤና ተቋማት መወሰዳቸውን ጠቁመዋል፡፡
 
የአደጋው መንስኤና ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ቁጥር እየተጣራ መሆኑንም አቶ ንጋቱ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.