Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ለመጪው ክረምት ከ19 ሚሊየን በላይ የቡናና ፍራፍሬ ችግኞች እየተዘጋጁ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በመጪው ክረምት የሚተከሉ ከ19 ሚሊየን በላይ የቡናና ፍራፍሬ ችግኞች እየተዘጋጁ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።
 
በቢሮው የአትክልትና ፍራፍሬ ባለሙያ አቶ ግርማ በቀለ እንደገለጹት÷ቢሮው አርሶ አደሩን ከሰብል ልማት ጎን ለጎን በቡናና ፍራፍሬ ልማት በማሳተፍ ተጠቃሚነቱን ለማረጋገጥ እየሰራ ነው።
 
ለዚህም በመጪው ክረምት የሚተከሉ ከ19 ሚሊየን በላይ የቡናና ፍራፍሬ ችግኞችን ለማዘጋጀት ታቅዶ እስካሁን 13 ነጥብ 5 ሚሊየን ችግኞች መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
 
እየተዘጋጁ ካሉት ችግኞች ውስጥ 8 ነጥብ 3 ሚሊየን የሚሆኑት የተሻሻለ ዝርያ ያላቸው የቡና ችግኞች መሆናቸውን አመልክተዋል።
 
ችግኞቹ አቮካዶ፣ ማንጎ፣ ፓፓያ፣ ዘይቱን፣ ሙዝ፣ ብርቱካን፣ አፕልና ጨምሮ ሌሎች የፍራፍሬ ችግኞች ያካትታሉ ብለዋል።
 
የችግኝ ማፍላት ስራው በመንግስት፣ በግል እና በማህበራት በተዘጋጁ የችግኝ ማፍያ ጣቢያዎች እየተከናወነ እንደሚገኝ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
 
ችግኝ የማፍላት ስራው የአርሶ አደሩን ዘላቂ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ምርታማነታቸው ከፍያለና የተሻሻሉ ዝርያዎች ላይ ያተኮረ መሆኑን ጠቁመዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.