Fana: At a Speed of Life!

በሐረሪ ክልል በቂ የዘይትና ስኳር ምርት እየቀረበ አይደለም ተባለ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ንግድ ልማት ኤጀንሲ በክልሉ በቂ የዘይት እና ስኳር ምርት እየቀረበ አለመሆኑን ገልጿል፡፡

በኤጀንሲው የማኅበራት ማደራጃ እና ፍትሐዊ ግብይት ንግድ ሥርዓት ዳይሬክተር መሐመድ ዩሱፍ እንዳሉት ÷ ለክልሉ የተመደበው ስኳር እና ዘይት በሸማች ኅብረት ሥራ ማኅበራት በኩል ለሕብረተሰቡ እየተሰራጨ ነው፡፡

ይሁን እንጂ በተለይም በጾም ወቅት ፍላጎት ስለሚጨምር እየቀረበ ያለው ምርት በቂ እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡

የረመዷን ጾም እና የትንሳዔ በዓላትን ታሳቢ በማድረግ በቂ አቅርቦት እንዲኖር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ በላይነሽ ረጋሳ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ÷ ከውጭ ሀገር የሚገባው የስኳር ምርት ሂደቱ ባለመጠናቀቁ እና በሀገር ውስጥ ያሉ የስኳር ፋብሪካዎች ላለፉት ሶስት ዓመታት በስኳር ኢንዱስትሪው ባጋጠሙ ተግዳሮቶች ምክንያት በያዝነው ዓመት የስኳር ፋብሪካዎች በመሉ አቅማቸው ወደ ምርት ባለመግባታቸው የምርት እጥረት መከሰቱን ገልጿል፡፡

ይህም ሆኖ ግን የተወሰኑ ፋብሪካዎች ወደ ምርት በመመለሳቸው ክልሎች ቀደም ሲል ያገኙት ከነበረው ምርት 25 በመቶ ጭማሬ መደረጉን ነው የሕዝብ ግንኙነትና ተሳትፎ ዋና ክፍል ኃላፊው ረታ ደመቀ ያረጋገጡት፡፡

በሌላ በኩል ከግብርና ቢሮ ጋር በመተባበር ያለምንም የደላላ ሰንሰለት አርሶ አደሮች ምርታቸውን በቅዳሜ እና እሁድ ገበያ በቀጥታ ለሸማች እያቀረቡ መሆኑን መሐመድ ዩሱፍ ገልጸዋል፡፡

ይህም ሕገ ወጥ ደላሎች ይፈጥሩት የነበረውን ውስብስብ ችግር በማስቀረት የኑሮ ውድነቱን በመቅረፍ የራሱን አስተዋጽኦ ማበርከቱን አመላክተዋል፡፡

ሕጋዊ የንግድ ሥርዓቱን ተላልፈው በተገኙ 89 የንግድ ተቋማት ላይም በሶስት ወራት ውስጥ እርምጃ መወሰዱን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አስረድተዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.