Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 19 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4 ሺህ 44 የላብራቶሪ 19 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው።

የጤና ሚኒስቴር ባወጣው የ24 ሰዓታት እለታዊ መግለጫ በሀገሪቱ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 306 መድረሱን አስታውቋል።

ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 15 ወንዶች እና አራት ሴቶች ናቸው።

በዜግነትም ሁሉም ኢትዮጵያውያን መሆናቸወን ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው።

ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሁለት ሰዎች ከአዲስ አበባ ሲሆኑ፥ 2 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል ጊንጪ ከተማ፣ ሶስት ሰዎች ከትግራይ ክልል ማይ ካድራና ሰቲት ሁመራ ለይቶ ማቆያ፣ አንድ ሰው ከአማራ ክልል መተማ ለይቶ ማቆያ እና 11 ሰዎች ከሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ለይቶ ማቆያ ናቸው።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው መካከል 15 ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው ሲሆን፥ ሁለቱ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው ናቸው። ቀሪዎቹ ሁለቱ ደግሞ የውጭ ሀገር ጉዞም ሆነ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው መሆናቸው ተመልክቷል።

በትናንትናው እለት አንድ ሰው ከኦሮሚያ ክልል ከበሽታው ያገገመ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 113 ደርሷል።

በአጠቃላይ በሀገሪቱ እስካሁን 53 ሺህ 29 ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ ተካሂዷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.