Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን በናይል ተፋሰስ አባል ሀገራት መካከል ጠንካራ ትብብር ሊኖር እንደሚገባ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የጋራ የሆነ ሀብትን በአግባቡ ለመጠቀም በናይል ተፋሰስ አባል ሀገራት መካከል ጠንካራ ትብብር ሊኖር እንደሚገባ ገለጹ፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን ከደቡብ ሱዳን የሽግግር ሥራ አስፈፃሚ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባዔ ጀማ ኑኑ ኩምባ ጋር በጁባ መክረዋል፡፡

የጋራ የሆነ ሀብትን በአግባቡ ለመጠቀም በናይል ተፋሰስ አባል ሀገራት መካከል ጠንካራ ትብብር ሊኖር እንደሚገባ አቶ ደመቀ በውይይቱ ላይ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵ ከደቡብ ሱዳን ጋር ያላትን ሁለንተናዊ ግንኙነት ለማጠናከር ፅኑ አቋም እንዳላትም አስረድተዋል፡፡

በኢትዮጵያ በኩል የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የበለጠ የሚያስተሳስሩ የመሰረተ ልማት ሥራዎችን ለማቀላጠፍ ቁርጠኝነት መኖሩንም ነው ያረጋገጡት፡፡

አፈ- ጉባዔ ጀማ ኑኑ ኩምባ በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያንና ደቡብ ሱዳንን በመሰረተ ልማት የማስተሳሰር ሥራ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው ማለታቸውን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

የሁለቱን ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ትስስር በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ያለንን ትብብር በይበልጥ ለማሣደግ የደቡብ ሱዳን መንግሥት ቁርጠኛ ነው ብለዋል፡፡

ለሁለት ቀናት በደቡብ ሱዳን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሲያደርጉ የቆየቱት አቶ ደመቀ መኮንን በጁባ የነበራቸውን ቆይታ አጠናቅቀው ተመልሰዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.