Fana: At a Speed of Life!

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በወሳኝ ጨዋታዎች ዛሬ ይመለሳል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከዓለም አቀፍ ጨዋታዎች መልስ ዛሬ ማንቼስተር ሲቲ ከሊቨርፑል በሚያደርጉት ወሳኝ ጨዋታ ይጀምራል፡፡

9፡30 ላይ በኢትሃድ በሚደረገው የሁለቱ ተፎካካሪ ቡድኖች ጨዋታ ማንቼስተር ሲቲ መሪነቱን ለማስጠበቅ ሊቨርፑል ደግሞ አሸንፎ መሪነቱን ለመረከብ ይፋለማሉ፡፡

የሊቨርፑሉ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ÷ ዛሬ የምናደርገው ጨዋታው የቀያዮቹ የሻምፒዮናነት መለያ አይደለም ብለዋል፡፡

በጨዋታው የማንቼስተር ሲቲው የፊት መስመር አጥቂ ኤርሊንግ ሃላንድ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ በደረሰበት የቁርጭምጭሚት ጉዳት የመሰለፉ ጉዳይ አጠራጣሪ ሆኗል፡፡

በተመሳሳይ ማቲዮ ኮቫችች፣ ሰርጂዮ ጎሜዝ እና ማቲው ኑኔዝ የመሰለፋቸው ጉዳይ አጠራጣሪ ሲሆን÷ ጆን ስቶንስ እና ኬቨን ዲ ብሮይን አሁንም ከጨዋታው ውጭ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡

በሊቨርፑል ምንም ዓይነት የተጨዋች ጉዳት ዜና ያልተሰማ ሲሆን÷ አሌክስ ማክ አሌስተር ኢብራሂማ ኮናቴ፣ ኮረቲስ ጆንስ፣ ሪያን ግራቨንበርክ እና ጆ ጎሜዝ በልምምድ ሜዳ ተግኝተዋል ተብሏል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች ባለፉት ሥድስት ጨዋታዎች በነበራቸው የእርስበርስ ግንኙነት ማንቼስተር ሲቲ አምሥቱን በማሸነፍ የበላይነቱን መያዙን ቢቢሲ ስፖርት አስነብቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.