Fana: At a Speed of Life!

ቻይና ከአሜሪካ ጋር ጤናማ ወታደራዊ ግንኙነት እንዲኖራት እንደምትሻ ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ከአሜሪካ ጋር ጤናማ እና በመከባበር ላይ የተመሠረተ ወታደራዊ ግንኙነት እንዲኖራት እንደምትሻ አስታወቀች፡፡

የቻይና መከላከያ ሚኒስቴር አቋሙን ያስታወቀው በዋሽንግተን በተሰናዳው 17 ኛው የሀገራቱ የመከላከያ ፖሊሲ ውይይት ላይ መሆኑን ሲጂቲ ኤን ዘግቧል፡፡

ሚኒስቴሩ÷ አሜሪካ በጦር ግንባር ያለው ኃይሏ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንድታደርግ እና የደኅንነት ጉዳዮችንም በጥንቃቄ እንድትመለከት አስገንዝቧል፡፡

አሜሪካ በደቡብ ቻይና ባሕር ያሰፈረችውን ወታደራዊ ኃይል እንድትቀንስና ከሌላ ወገን የሚመጣ ጠብ-አጫሪ ተግባርም መደገፏን እንድታቆም ጠይቋል፡፡

አሜሪካ በተለይ የባሕር እና የዓየር ኃይል የደኅንነት ጉዳዮች ምን ያኅል ትኩረት የሚሹ እንደሆኑ ተገንዝባ ወታደሮቿን በሥነ-ምግባር ማነፅ እንዳለባትም አመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.