Fana: At a Speed of Life!

አንጎላ ናሚቢያን በማሸነፍ  ሩብ ፍጻሜው ተቀላቀለች

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ አንጎላ ናሚቢያን 3 ለ 0 በማሸነፍ ወደ ሩብ ፍጻሜው ገብታለች፡፡

ምሽት 2 ሰዓት ላይ በቡዋኬ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አዲልሰን ነቡላ፣ ጊልሰን ዳላ እና ኦገስቲኖ ሙቡሉ ለአንጎላ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል፡፡

በጨዋታው የአንጎላው ግብ ጠባቂ አዲልሰን ኔብሉ እና የናሚቢያው ተጫዋች ሉቤኒ ሁዋኮንጎ በሜዳ ውስጥ በፈፀሙት ጥፋት በቀይ ካርድ ከሜዳ ተወግደዋል፡፡

የአፍሪካ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ምሽት ሲካሄድ ምሽት ናይጀሪያ ከካሜሮን የሚደርጉት ወሳኝ ጨዋታ ተጠባቂ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.