Fana: At a Speed of Life!

የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀቁ

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ14ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ዛሬ የተካሄዱ ሁለት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቅቀዋል፡፡

ቀን 9 ሰዓት አዳማ ከተማ ከፋሲል ከነማ ያደረጉት ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡

የፋሲል ከነማን ብቸኛ ግብ ጌታነህ ከበደ ሲያስቆጥር÷ሲቦና ዓሊ ደግሞ ለአዳማ ከተማ አስቆጥሯል፡፡

ምሽት 12 ሰዓት ላይ ሻሸመኔ ከተማ ከድሬዳዋ ከተማ ያደረጉት ጨዋታም በተመሳሳይ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡

ግቦቹንም አለን ካይዋ ለሻሸመኔ ከተማ ሲያስቆጥር÷ ሱራፌል ጌታቸው ደግሞ ለድሬዳዋ ከተማ አስቆጥሯል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.