Fana: At a Speed of Life!

የሸገር ደርቢ ጨዋታ ለመጀመሪያ ጊዜ በዱባይ ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 04፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና ጨዋታ ለመጀመሪያ ጊዜ በተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ዱባይ ከተማ እንደሚካሄድ ክለቦቹ አስታውቀዋል፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና ክለቦች በሰጡት መግለጫ ÷በመጪው የካቲት 16 ቀን 2016 ዓ.ም በዱባይ ከተማ ጨዋታቸውን እንደሚያካሂዱ ገልጸዋል፡፡

የሁለቱ ክለቦች የስፖርት ማህበራትም ከየካቲት 14 እስከ 17 ቀን  2016 ዓ.ም ድረስ በሚኖራቸው ቆይታ የገቢ ማስገኛ ፕሮግራሞችን  እንደሚያከናወኑ ተመልክቷል።

ውሳኔው ክለቦቹ ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን እንዲያገኙ ለማስቻልና  በዘርፉ የኢትዮጵያና የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶችን  ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ  ነው ተብሏል ።

የሁለቱ ክለቦችደርቢ ጨዋታ በቴሌቪዥን  የቀጥታ ስርጭት እንደሚኖረውም  በመግለጫው ተጠቁሟል፡፡

በወርቅነህ ጋሻሁን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.