Fana: At a Speed of Life!

ጋዜጠኛ አንቷን ጋሊንዶ በቁጥጥር ሥር የዋለው ከተሰጠው የዘገባ ፈቃድ ውጪ ሲንቀሳቀስ በመገኘቱ ነው – የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፈረንሳዊው ጋዜጠኛ አንቷን ጋሊንዶ በቁጥጥር ሥራ የዋለው ከተሰጠው የዘገባ ፈቃድ ውጪ በሀገር ውስጥ ጉዳይ ዘገባ ለመስራት ሲንቀሳቀስ በመገኘቱ ነው ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ በሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም ጋዜጠኛ አንቷን ጋሊንዶ ለ37ኛው አፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ የዘገባ ሽፋን ለመስጠት ፈቃድ አግኝቶ ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱን አስታውሰዋል፡፡

ይሁን እንጂ ግለሰቡ የጋዜጠኝነት ሙያን ሽፋን በማድረግ አዲስ አበባ ከገባበት ቀን ጀምሮ ከመጣበት ዓላማ ፍጹም ተቃራኒ የሆኑ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን የሚሳዩ መረጃዎች መገኘታቸውን አንስተዋል፡፡

ይህም ከመጣበት አላማ ውጪ በተለይም የኢትዮጵያን ውስጣዊ የፖለቲካ ጉዳዮችን የተመለከቱ መረጃዎችን ለመሰብሰብ ሲሞከር እንደነበር አብራርተዋል፡፡

በዚህም የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች እና አባላትን እንዲሁም የፖለቲካ ተሳትፎ አላቸው ያላቸውን ማህበራዊ አንቂዎችን ሲያነጋግር እንደነበር ገልጸዋል፡፡

ግለሰቡ ወደ ኢትዮጵያ ከመጣበት ዋነኛ ዓላማ ውጪ በሀገሪቱ ውስጣዊ ጉዳይ ላይ ትኩረት በማድረግ መረጃዎችን ለመሰብሰብ ባደረገው ጥረት ተጠርጥሮ የካቲት 14 ቀን በቁጥጥር ስር ውሎ ጉዳዩ በፍርድ ቤት እየታየ መሆኑን አስገነዝበዋል፡፡

ግለሰቡ በ24 ሰዓታት ውስጥ ፍርድ ቤት መቅረቡንም ነው ሚኒስትር ዴዔታዋ ያስረዱት፡፡

ለአፍሪካ ህብረት ዘገባ ፈቃድ የሚሰጠው ማንኛውም ጋዜጠኛ ከመጣበት ዓላማ ውጪ መስራት ህገ ወጥ እንደሆነ ጠቁመው÷ ይህም በየትኛውም ዓለም ያለ ሕግ መሆኑን አንስተዋል፡፡

የግለሰቡን ጉዳይ በተለያየ መልኩ ከሙያው እና ከዜግነቱ ጋር በማገናኘት የሚሰራጩ መረጃዎች ትክክል አለመሆናቸውንም አረጋግጠዋል፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.