Fana: At a Speed of Life!

አቶ አህመድ ሽዴ 20ኛውን የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ የሚኒስትሮች ስብሰባ መሩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የወቅቱ የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ ሊቀ መንበር የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) እና ዓለም ባንክ ስብሰባ ጎን ለጎን 20ኛውን የምስራቅ አፍሪካ ኢኒሼቲቭ የሚኒስትሮች ስብሰባ መርተዋል፡፡

በዋሽንግተን ዲሲ በተካሄዳው ስበሰባ የዓለም ባንክ የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት የሆኑት ቪክቶሪያ ክዋክዋ ከአቶ አህመድ ሽዴ ጋር በመሆን በስብሰባው ተገኝተዋል፡፡

በስበሰባው የአፍሪካ ቀንድ የገንዘብ ሚኒስትሮች፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ እና የዓለም ባንክ ተወካዮች እንዲሁም የጀርመን እና ብሪታኒያ ተወካዮች ተሳትፈዋል፡፡

በ20ኛው የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ የሚኒስትሮች ስብሰባ የአረብ ባንክ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ልማት፣ የሳዑዲ ልማት ፈንድ፣ የአሜሪካ እና የጃፓን ልዩ መልዕክተኛ በአጋርነት መሳተፋቸውም ተመላክቷል፡፡

አዳዲስ ተቋማት በኢኒሼቲቩ መሳተፋቸውን ያደነቁት አቶ አህመድ፤ የምስራቅ አፍሪካ ኢኒሼቲቭ ባዘጋጀው ህጋዊ ማዕቀፍ ውስጥ ተካተው መደበኛ አጋር እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ኢኒሼቲቩ ባለፉት አምስት አመታት ሀብት በማሰባሰብ ረገድ ስኬታማ እንደነበር አስታውሰው፤ ይህ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አፅዕኖት ሰጥተዋል፡፡

የምስራቅ አፍሪካ ኢንሼቲቭ ሰባት የአፍሪካ ቀንድ ሀገራትን በአባልነት አካትቶ በፈረንጆቹ 2019 የተመሰረተ ሲሆን በቀጠናው ኢኮኖሚያዊ ውህደትን ለማጠናከር እየሰራ እንደሚገኝ የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.