Fana: At a Speed of Life!

“ጽዱ ጎዳና – ኑሮ በጤና” የከተማ ውበትን በመጨመር ጤናማ አካባቢን የሚፈጥር ነው -ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ“ጽዱ ጎዳና – ኑሮ በጤና” ተግባር ነዋሪዎችን በሚያሳፍር መልኩ በየመንገዱ ከመፀዳዳት ይልቅ፣ የከተማ ውበትን በሚጨምር መልኩ ጤናማ አካባቢን ለመፍጠር የሚያስችል ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ከንቲባዋ በማህበራ ትስስር ገጻቸው÷ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በገበታ ለሸገር እንዲሁም በተለያዩ የከተማዋ የልማት ስራዎች ሃሳብ ከማመንጨት ጀምሮ ፕሮጀክቶቹን ወርዶ በመምራት አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ እና ፅዱ ለማድረግ በርካታ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተማዋን ውብ፣ ፅዱና ለነዋሪዎቿ ምቹ የማድረግ ራዕያቸው አካል የሆነ “ጽዱ ጎዳና – ኑሮ በጤና” የሚል አዲስ ሃሳብ የአፍሪካውያን መዲና በሆነችው አዲስ አበባ ጀምረዋልም ነው ያሉት፡፡

ተግባሩ ነዋሪዎችን በሚያሳፍር መልኩ በየመንገዱ ከመፀዳዳት ይልቅ፣ የከተማ ውበትን በሚጨምር መልኩ፣ ጤናማ አካባቢንም ለመፍጠር የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡

“ለነዋሪዎቿ ምቹ ከተማ ለመፍጠር ጠቅላይ ሚኒስትራችን በጀመሩት ተግባር ላይ ከማንም በላይ መላው አመራራችን እና ተጠቃሚ የሆኑ የከተማችን ነዋሪዎች በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪ ማስተላለፍ እወዳለሁ” ሲሉ ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.