Fana: At a Speed of Life!

በአዳማ ከተማ በአፈር መደርመስ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዳማ ከተማ ለሕንፃ ግንባታ ጉድጓድ በመቆፈር ላይ በነበሩ ሰራተኞች ላይ አፈር ተደርምሶ የሁለት ሰራተኞች ህይወት ማለፉን የከተማው ዋና ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡

በመምሪያው የኮሙኒኬሽን ኃላፊ ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ እንደገለጹት÷አደጋው ትናንት በከተማው ደጋጋ ወረዳ ልዩ ቦታው ቀጠና አራት አካባቢ የደረሰ ነው፡፡

በአደጋው ህይወታቸው ካለፉት በተጨማሪም ሌሎች ሁለት የጉልበት ሰራተኞች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸው የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ሀላፊው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

ሕንፃ አሰሪዎች ለሚያሰሯቸው ሰራተኞች የስራ ደህንነት ሊጠብቁና ዋስትና ሊሰጡ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

በኤርሚያስ ቦጋለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.