Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የተንጸባረቀው ሀሳብ ትክክል ያልሆነና ተቀባይነት የሌለው ነው – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የተንጸባረቀው ሀሳብ ትክክል ያልሆነና ተቀባይነት የሌለው ነው ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር በትናንትናው ዕለት ያደረጉት ንግግር በተረጋገጠ መረጃ ላይ ያልተመሰረተና በምርጫ ወደ ስልጣን የመጣን መንግስት እንጥላለን በሚል የሚንቀሳቀሱ፣ ንጹሃንን ከሚያግቱና ከሚያሸብሩ አካላት ጋር መንግስትን መጥቀሳቸው ተገቢ አለመሆኑን አስታውቋል፡፡

የአምባሳደሩ ንግግር የኢትዮጵያ መንግስት ሀገሪቷን እንዴት መምራት እንዳለበት ያልተጠየቀ ምክር ለመመምከር የሞከረ ነው ሲልም ገልጿል፡፡
የአምባሳደሩ መልዕክት ከሁለቱ ሀገራት ታሪካዊና ወዳጅነት ላይ ከተመሰረተው ግንኙነት የተቃረነ እንደሆነም ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።

ኢትዮጵያና አሜሪካ ግንኙነታቸውን አጠናክረው በመቀጠል በብሔራዊ፣ ቀጣናዊና የጋራ በሆኑ ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ መስራታቸውን እንደሚሰሩ ጠቅሶ፤ ኢትዮጵያ የሰላምና የጸጥታ ጉዳዮችን ጨምሮ ከአሜሪካ ጋር ለመስራት ያላትን ዝግጁነት ገልጿል።

ሚኒስቴሩ በአዲስ አበባ ከሚገኘው ኤምባሲ ጋር በመስራት የተፈጠረውን ስህተት እንዲታረም የሚያደርግ መሆኑን አመልክቶ፤ የተፈጸመውን ዲፕሎማሲያዊ ስህተት ማረም እንደሚገባ ጠቁሟል።

ኢትዮጵያ በመከባበር ላይ የተመሰረተ የሁለትዮሽ ግንኙነትና ትብብር እንዲኖር ቁርጠኛ መሆኗንም መግለጫው አረጋግጧል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.