Fana: At a Speed of Life!

በፌዴራል ድጎማ በጀት ክፍፍል ቀመር ላይ የተደረገውን ጥናት፤ ልዩ ዓላማ ያለው የድጎማ በጀት የሚከፋፈልበትን የአሰራር ስርዓት ላይ ውይይት እየተካሄ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በፌዴራል ድጎማ በጀት ክፍፍል ቀመር ላይ የተደረገውን ጥናት፤ ልዩ ዓላማ ያለው የድጎማ በጀት የሚከፋፈልበትን የአሰራር ስርዓት ላይ ውይይት እየተካሄ ይገኛል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የተሰጠውን ሕገ መንገስታዊ ተልዕኮ በብቃት ለመዋጣት በጥናት ላይ የሚገኘውን የምክርቤቱ ሪፎርም በ4 ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ በማተኮር የግብዓት መሰብሰብ መድረክ በዛሬው ቀን በአዲስአበባ ከተማ እያካሄደ ነው።

ሀገራዊ አንድነት እና ዘላቂ ሰላም መገንባት፣ ውጤታማ የፊሲካል ሽግግርና ፍትሐዊ የሃብት ክፍፍል ፣ የሕገ መንግሥት የበላይነትና ሕገ መንግስታዊነት ማረጋገጥ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት በሕግ መንግሥቱ የተሰጡ ስልጣንና ተግባራትን ናቸው ተብሏል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ  አቶ አደም ፋራህ በምክር ቤቱ የተጀመረው ተቋማዊ ሪፎርም በሀገሪቱ የተመጣጠነ እድገት ለማስመዝገብና ሕብረብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር ስለሚረዳ  በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ሌሎች በዘርፉ ከፍተኛ ልምድና እውቀት ባላቸው የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሙያዎች ጥናት እያስጠና እንደሚገኝ ገልጸዋል።

አፈ ጉባዔው፤ የፊሲካል ሽግግርና ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል ፣ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትንና እኩል የመልማት እድልን በማረጋገጥ ሀገራዊ አንድነትን ለመገንባት ያላው አስተዋጽኦ ትልቅ መሆኑን አንስተዋል።

በመሆኑ አሁን በሥራ ላይ ያለውን የድጎማ ማከፋፈያ ቀመር ክፍተቶችን በጥናት በመለየት ለቀጣይ ቀመር ዝግጅት በግብዓትነት መጠቀም፣ የፌዴራል መሰረተ ልማት ሥርጭት ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ የክትትል ሥርዓትና የማስፈጸሚያ ስልቶችን ማዘጋጀት፣ የድጎማ ቀመሩ በክልሎች መካከል የተመጣጠነ እድገት እና ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍልን በማረጋገጥ ረገድ ያለውን ሚና የመገምገምና የማሻሻያ ሥርዓት ማበጀት በጣም አስፈላጊ ነው ብለዋል።

ይህንን ዓላማ ለማሳከት የፌዴሬሽን ምክር ቤት በልዩ ትኩረት እየሰራ እንዳሚገኝ በመግለፅ እስከ አሁንም በተሰራ ስራ አበረታች ጅማሮ እንዳለና ይህንን ጅማሮ በጥናት መደገፍ አስፈላጊነቱ መሆኑን ተናግረዋል።

በተጨማሪም ክልሎች ለወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ድጎማ የሚሰጡበት ሥርዓት የሚስተካከልበትን ሁኔታ መፍጠር፣ ልዩ ዓላማ ያላቸው የፌዴራል ድጎማዎች ግልጽነት፣ ተጠያቂነትና ዘላቂነት ባለው መልኩ በፍትሃዊነት ለክልሎች የሚከፋፈልበትን ሥርዓት መበጀት እና ለፊሲካል ሽግግር ውጤታማነት የመረጃ ሥርዓት መዘርጋት እንዲሁም የአፈጻጸም ስልት ማዘጋጀት በጥናቱ መካተቱን አፈ ጉባዔው መግለፃቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ጥናቶቹ የፌዴሬሽን ምክር ቤትን ሕገ መንገስታዊ ተልዕኮን መነሻ በማድረግ የተዘጋጁ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን በዛሬው መድረክ ከተሳታፊዎች የሚቀርቡ ገንቢ ግብዓቶችን በማካተት የጥናት ሰነዶቹን  በማዳበር የጥናት ውጤቶችንና ጠቃሚ ምክር ሀሳቦችን መሰረት በማድረግ የተለያዩ የአሠራር ሥርዓቶች የሚዘረጉና ተቋማዊ የሚሆኑበት ሁኔታ ይፈጠራል ተብሏል።

በመድረኩ ላይ የክልሎች ርዕሳነ መስተዳድራን፣ የክልል ቢሮ ኃላፊዎችና የፌዴራል ከፍተኛ አመራሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.