Fana: At a Speed of Life!

ለአትሌቶች እና አሰልጣኞች ሽልማት ተበረከተ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የደቡብ ክልል መንግስት በቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ ሜዳልያ ላስገኙ አራቱ አትሌቶች እና አሰልጣኞች ማበረታቻ ሽልማት አበረከተ ።

ለሰለሞን ባረጋ 500ሺህ ብር፣ 10ሺህ ካሬሜትር በወልቂጤ ከተማ የኢንቨስትመንት ቦታ እንዲሁም የማዕረግ እድገት ተሰጥቶታል፡፡

ለአትሌት ለሜቻ ግርማ 350 ሺህ ብር፣ ለአትሌት ለተሰንበት ግደይ እና ለአትሌት ጉድፍ ጸጋዬ ለእያንዳንዳቸው 250ሺህ ብር ተበርክቶላቸዋል፡፡

ለአሰልጣኝ ሁሴን ሽቦ፣ ለአሰልጣኝ ተሸመ ከበደ፣ ለአሰልጣኝ ሃይሌ እያሱ እና ለአቶ እሉፍ ይህደጎ 100ሺህ ብር ተበርክቶላቸዋል፡፡

ለአሰልጣኝ ኮማንደር ቶሌራ ዲንቃ እና ኢንስፔክተር ኢብርሂም ዳኜ 50 ሺህ ብር ተበርክቶላቸዋል፡፡

በተጨማሪም ለእያንዳንዳቸው የ1ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ተሰጥቷቸዋል፡፡

በፀጋዬ ወንድወሰን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.