Fana: At a Speed of Life!

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጊዜ ቀጠሮ ችሎት በእነ ዶክተር አዲስዓለም ባሌማ የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ገለልተኛ አስተዳዳሪ እንዲሾም ወሰነ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጊዜ ቀጠሮ ችሎት በእነ ዶክተር አዲስዓለም ባሌማ የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ገለልተኛ አስተዳዳሪ እንዲሾም ወሰነ፡፡

ችሎቱ ውሳኔውን ያሳለፈው ዐቃቤ ሕግ በወንጀል የተገኘ ንብረት ወይም ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ  መጠቀም እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀል መጠርጠራቸውን ተከትሎ በስማቸው ተመዝግቦ ተንቀሳቃሽ ያልሆነ ንብረት በሚል የተመዘገበው መኖሪያ ቤት ይታገድልኝ በማለት ባቀረበው አቤቱታ ነው፡፡

ዐቃቤ ሕግ በአቤቱታው ከዚህ ከተከሳሹ ቤት የሚገኝ የኪራይ ገቢ ለሽብር ተልዕኮ እየዋለ መሆኑንና ሕጉ በሚፈቅደው መሰረት ንብረቱ በገለልተኛ ወገን እንዲተዳደር ይደረግ በማለት አመልክቷል፡፡

ተከሳሹ ይህ ሊሆን አይገባም በማለት የተከራከረ ሲሆን ዐቃቤ ሕግም ምላሽ ሰጥቷል፡፡

የግራ ቀኙን ክርክር የመረመረው ችሎቱ የተከሳሹን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ ቤቱ ገለልተኛ አስተዳዳሪ እንዲሾምለት ውሳኔ መስጠቱትን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.