Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት  ከፍተኛ ዋጋ የሚያወጡ ትላልቅ ኬብሎችና ለጥፋት ተልዕኮ የሚጠቀሙባቸው የተለያዩ ቁሳቁሶች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በአዲስ አበባ ከተማ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ ከፍተኛ ዋጋ የሚያወጡ ትላልቅ ኬብሎችና  ለጥፋት ተልዕኮ የሚጠቀሙባቸው የተለያዩ ቁሳቁሶች ተያዙ።

ለኮንዶሚኒየም ቤቶችና ለግዙፍ መሰረተ ልማት ግንባታዎች የሚዘረጉ የኃይል ማስተላለፊያዎችን ጨምሮ ከፍተኛ ዋጋ የሚያወጡ በርከት ያሉ የተለያዩ ኬብሎች ለጥፋት መፈፀሚያ ከሚውሉ የተለያዩ ቁሳቁሶች ጋር በአዲስ አበባ ኮልፌ ወረዳ 2 ልዩ ስሙ ሙሉ ወንጌል ካራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ በድብቅ ተከማችተው መገኘታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል ፡፡

በግለሰቡ መኖሪያ ቤት ውስጥ በቁጥጥር ስር የዋሉት ኬብሎች አብዛኞቹ ምድር ለምድር የሚዘረጉና በተደራጃ ስርቆት ተቆፍረውና በተለያዩ መቁረጫዎች ተቆራርጠው የወጡ መሆናቸውን በዋጋ ደረጃም ከፍተኛ ከመሆናውም በላይ መንግስትንም ሆነ ተቋማትን ለኪሳራ የሚዳርጉ መሆናቸው በመግለጫው ተጠቁሟል፡፡

በዚህ የተደራጀ ዘረፋ ውስጥ የተሳተፉ ግለሰቡን ጨምሮ ሌሎች ተጠርጣሪዎችንም በቁጥጥር ስር ለማዋል በተደረገው ኦፕሬሽን የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ኦፊሰሮች ጥብቅ ሚስጥራዊ ክትትል በማድረግ እንዲሁም የአዲስ አበባ ፖሊስ ግለሰቦችን በመያዝ መሳተፋቸውን መግለጫው አመልክቷል፡፡

በተያያዘ ከቡራዩ ወደ ወለጋ ለሸኔ የሽብር ቡድን በጭነት መኪና በሚስጥር ተቀምጦ ሊጓጓዝ የነበረ 300 የክላሽንኮቭ ጥይት በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ኦፊሰሮችና በአዲስ አበባ ፖሊስ በጋራ በተደረገ ክትትል እጅ ከፍንጅ መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል ሲል ኢፕድ ዘግቧል፡፡

ከሽብርተኛው የሸኔ ቡድን ጋራ በህቡእ በመገናኘት ጥይቶቹን በድብቅ ሊያስተላልፉ የሞክሩ ሶስት ተጠርጣሪዎች ቡራዩ ላይ በቁጥጥር ስር መዋላቸውም በ መግለጫው ተመላክቷል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.