Fana: At a Speed of Life!

ችግሮችን ተጋፍጦ ወደ እድል መቀየር በዓለማችን ላይ የሚገኙ ብርቅዬ ሴቶች መለያ ነው-ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ከአዲስ አበባ ከተማ ለተወጣጡ ሴቶች የሕይወት ልምዳቸውን አካፍለዋል።

“የሕይወት ልምዴን አካፍላለሁ ” በሚል መሪ ቃል ውጤታማ ሴቶች የህይወት ልምዳቸውን የሚያካፍሉበትና ሴቶች በሀገር ግንባታ ስለሚኖራቸው   ተሳትፎ እና ሚና በተመለከተ ውይይት ተካሂዷል ።

በዉይይት መድረኩ ተገኝተው የህይወት ልምዳቸውን ያካፈሉት ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ፥ ሴቶች ችግሮችን ተጋፍጦ መፍታት እንጂ መሸሽ ውጤት አያመጣም ያሉ ሲሆን  ለዚህም ሴቶች ችግሮችን የመፍታት እና የመጋፈጥ ልምዳችንን ማዳበር ይኖርብናል ብለዋል ።

ችግሮችን ተጋፍጦ ወደ እድል መቀየር በዓለማችን ላይ የሚገኙ ብርቅዬ ሴቶች መለያ በመሆኑ በራስ መተማመንን ማዳበር፣ ችሎታን መለየትና እችላለሁ ብሎ መሞከር ሴቶችን ለተሻለ ስኬት ሊያበቃቸው ይችላል ብለዋል።

ወደ ለዉጥና ስኬት ለመድረስ ሴቶች ውስብስብ ፈተናዎችን ተጋፍጠው ማለፍ እንደሚጠበቅባቸው የገለፁት ምክትል ከንቲባዋ ገልጸዋል።

ችግሮች ሲያጋጥሙ ሌሎችን ከመውቀስ ይልቅ መፍትሔው ላይ ጊዜያችሁን ማጥፋት ይኖርባችኋል ያሉት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፥ ከሌሎች ጠንካራ ሰዎች  የሕይወት ልምዶችን በመቅሰም ለጉዟችሁ እንደ ስንቅ መጠቀም አለባችሁ ሲሉ መልዕክት  ማስተላለፋቸውን ከከተማአስተዳደሩ ፕሬስ ሰክሬተሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.