Fana: At a Speed of Life!

የሀይማኖት ተቋማት ሰላምን በማስፈን ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከሁሉም የእምነት ተቋማት የተውጣጡ የሀይማኖት አባቶች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እየተወያዩ ነው፡፡

ውይይቱ በአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አዘጋጅነት “ሀይማኖታዊ የጋራ እሴቶች ለሰላም እና ለሀገራዊ አንድነት”በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

የእምነት ተቋማት ፣መሪዎች፣ አባቶች እና መምህራን ትውልድን በመቅረጽ፣ የህብረተሰብ ትስስር በማጠናከር ፣ ሀገራዊ አንድነትንና ህዝብን ከህዝብ የሚከፋፍሉ እኩይ ተግባራትን እንዲጸየፉ ለተከታዮቻቸው ሊያስተምሩ እንደሚገባ በውይይት መድረኩ ተገልጿል፡፡

የሀይማኖት ተቋማት ሀገሪቱ አሁን ያለችበትን አስቸጋሪ ሁኔታ እንድትሻገር እና ሰላም እንዲሰፍን ተገቢውን ስራ በመስራት የሀገርን ህልውና በማስጠበቅ ረገድም ሚናቸውን በአግባቡ ሊወጡ ይገባል መባሉን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይን የተመለከተው የውይይት መድረክ ከትናንት ጀምሮ ነው እየተካሄደ ያለው።

መድረኩ ለሀገርና ለህዝብ ህልውና የሃይማኖት ተቋማት ሚና ፣ፐብሊክ ዲፕሎማሲና የዜጎች ተሳትፎና አስተዋጽኦ እና ሀሰተኛ መረጃዎች ስርጭትና አሉታዊ ተጽእኖ በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች እየተካሄደ ነው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.