Fana: At a Speed of Life!

ከ19 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ወታደራዊ ትጥቅ ለመከላከያ ሠራዊት ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለሃገር መከላከያ ሠራዊት ከ19 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ወታደራዊ ትጥቅ አበረከተ።
የኮርፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል አህመድ ሃምዛ ወታደራዊ ትጥቁን ለመከላከያ ህብረት ሎጂስቲክስ ዋና መምሪያ ሃላፊ ተወካይና የመከላከያ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ ብርጋዴር ጄኔራል አስረስ አያሌው አስረክበዋል።
የወታደራዊ ትጥቅ ድጋፉ ሠራዊቱ የሕልውና ማስከበር ዘመቻውን በብቃት መወጣት እንዲችል የተደረገ መሆኑ ተገልጿል።
ኢትዮጵያ በሚገጥሟት ፈተናዎች አንድም ጊዜ ሸብረክ ብላ አታውቅም ያሉት ሜጀር ጄኔራል አህመድ ሀምዛ ከውስጥም ሆነ ከውጭ የተጋረጡባትን ፈተናዎች በድል ትሻገራለች ብለዋል።
ብርጋዴር ጄኔራል አስረስ አያሌው በበኩላቸው ÷ኢትዮጵያን እየፈተኗት ያሉት በራሷ ሀብት የበለፀጉ ባንዳዎች መሆናቸውን ተናግረዋል።
የህወሓት ቡድን ከውጭ ጠላቶች ጋር በማበር ኢትዮጵያን ለማፍረስ እየሰራ መሆኑን አስታውሰው ይህን ቡድን ለአንድና ለመጨረሻ ጊዜ ማጥፋት ይገባል ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
ብርጋዴር ጄኔራሉ ኮርፖሬሽኑ ላበረከተው የወታደራዊ ትጥቅ ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.