Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ወሎ ዞን የዘማች አርሶ አደሮችን የእርሻ መሬት የመንከባከብ ስራ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ በ1 ሺህ 333 ሄክታር የዘማች አርሶ አደሮች የእርሻ መሬት ላይ የአረም ነቀላና የእንክብካቤ ስራ እየተሰራ መሆኑን አስታወቀ፡፡
የዞኑ ግብርና መምሪያ ምክትል ሀላፊ አቶ አሊ ሰይድ እንደገለፁት÷ በዞኑ ከ6 ሺህ በላይ ዘማች ቢኖርም የ2 ሺህ 822 ዘማቾች የእርሻ መሬት ከዘር ስራ እስከ አረም ነቀላ በተገቢው መንገድ እተከናወነ ነው፡፡
የዘማች ቤተሰቦችን ከመንከባከብና ከእርሻ በተጨማሪም ሌሎች የሚያስፈልጋቸውን ስራ በተገቢው መንገድ እየተሰራ እንደሚገኝም ተገልጿል፡፡
በዞኑ ከወረዳ እስከ ቀበሌ አርሶ አደሩ መሰረታዊ የውትድርና እውቀት እንዲኖረው የተደረገ ሲሆን÷ በዚህም አካባቢን ነቅቶ በመጠበቅ ከሰር ጎገቦች የማፅዳት ስራ እየተከናወነም ነው ተብሏል፡፡
በኢሳያስ ገላው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.