Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ ለህንድ የምትሸጠውን ኤስ 400 የሚሳኤል መቃወሚያ ማምረት ጀመረች

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ ለህንድ ለመሸጥ የተስማማችውን ኤስ 400 የሚሳኤል መቃወሚያ ማምረት ጀምራለች።

ህንድ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2018 ኤስ 400 የተሰኘውን የሚሳኤል መቃወሚያ ከሩሲያ ለመግዛት መስማማቷ ይታወሳል።

በዚህ መሰረትም ህንድ ከሩሲያ 5 ነጥብ 4 ቢሊየን  ዶላር ዋጋ የሚያወጡ አምስት ኤስ 400 የሚሳኤል መቃወሚያዎችን ለመግዛት ውል ፈፅማለች።

ይህን ተከትሎም አሜሪካ  ኒው ዴልሂ ከሞስኮ የሚሳኤል የመቃወሚ ለመግዛት የፈጸመችውን ስምምነት  እንድትሰርዝ ስታስጠነቅቅ ቆይታለች።

ህንድ ስምምነቱን የማትሰርዝ ከሆነም አሜሪካ በሀገሪቱ ላይ የተለያዩ ማዕቀቦችን እንደምትጥል አስታውቃለች ።

ይሁን እንጂ ህንድ የዋሽንግተንን ማስፈራሪያ ወደ ጎን በመተው ከሩሲያ ጋር የተስማማችውን የሚሳኤል መቃወሚያ ግዥ በስምምነቱ መሰረት እንደምትፈፅም ገልጻለች።

ሩሲያ በበኩሏ ÷ በስምምነቱ በተያዘው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የመከላከያ ሚሳኤሉን ለህንድ ለማስረከብ ስራ መጀመሯን አስታውቃለች።

 

 

ምንጭ፦ https://www.rt.com/new

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.