Fana: At a Speed of Life!

ሽልማቱ የኔ አይደለም የመላው ኢትዮጵያውያን ነው- ክቡር ዶ/ር ኦባንግ ሜቶ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ  ለሰብዓዊ መብት ተሟጋች ኦባንግ ሜቶ የክቡር ዶክተሬት ሰጥቷል፡፡

በእውቅና ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት  ኦባንግ  ሜቶ ሽልማቱ ከጎኔ አብረውኝ ለነበሩ እና ለመላው ኢትዮጵያውያን ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ የብዙ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች መገኛ እንደሆነች የተናገሩት ክቡር ዶ/ር ኦባንግ ሜቶ፥ ባለፉት ጊዜያት ከነበረው ከፋፋይ ስርዓት በመላቀቅ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ወደ አንድነት እንዲመጡ ምክረ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በውስጥም በውጭም የሚደርስባትን ጫና ተቋቁማ  የጀመረችውን የልማት እና የዲሞክራሲ ግንባታ ስርዓት እንደምታጠናክር ዶ/ር ኦባንግ ገልፀዋል፡፡

ወደ ትክክለኛ ማንነታችን እንመለስ ያሉት ኦባንግ ሜቶ የአባይ ምንጭ መገኛ የሆንን የተጋመድን ወንድማማች ህዝቦች ነን፡፡

የስልጣኔ፣ የአንድነት፣ የሰብዓዊነት እና  የመተባበር  ኢትዮጵያዊነት ከፍታ ላይ እንቀመጥ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል::

ተመራቂ ተማሪዎችም ተመርቀው ከወጡ በሁዋላ የሃገሪቱን አንድነት ለመጠበቅ በሚደረገው ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.