Fana: At a Speed of Life!

ዲፕሎማትነት የአገር ብሔራዊ ጥቅምን ማስጠበቅ የሚያስችል ክህሎትና እውቀት የሚጠይቅ ተልዕኮ ነው- ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 11፤ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)ዲፕሎማትነት በከባድ ሁኔታ ውስጥም ሆኖ የአገር ብሔራዊ ጥቅምን ማስጠበቅ የሚያስችል ክህሎት እና እውቀት የሚጠይቅ ተልዕኮ ነው ሲሉ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተናገሩ፡፡
ፕሬዚዳንቷ የውጭ ጉዳይ ዋናው መስሪያ ቤት ሰራተኞች፣ አምባሳደሮች፣ ዲፕሎማቶች፣ ተጠሪ ተቋማት፣ ከሀገር መከላከያ ሚኒስቴር እና ከተለያዩ ተጠሪ ተቋማት ለተውጣጡ ባለሙያዎች የህይወት ተሞክሯቸውን እና ልምዳቸውን አካፍለዋል።
ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዲፕሎማቶች በተሠማሩባቸው ተልዕኮዎች ሁሉ ኢትዮጵያ ያለችበትን ቀጣናዊ ሁኔታ በየጊዜው መረዳት እና ከግንዛቤ ውስጥ ማስገባት አለባቸው ነው ያሉት።
የሀገር ፍቅር፣ የዓላማ ፅናት፣ ለሁሉን አቀፍ እውቀት ክፍት መሆን እና በየጊዜው ራስን እያሻሻሉ መንቀሳቀስ ከዲፕሎማቶች የሚጠበቅ መሆኑን አብራርተዋል ።
የዲፕሎማሲ ሥራ በአንድ አቅጣጫ ብቻ የሚከወን አለመሆኑን በመረዳት በታማኝነት እና በቁርጠኝነት ወቅቱ የሚጠይቀውን ክህሎት በመታጠቅ መንቀሳቀስን እንደሚጠይቅ ከረዥም የሥራ ልምዳቸው አጣቅሰው ፕሬዝዳንቷ መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
99
Engagements
Boost Post
92
7 Shares
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.