Fana: At a Speed of Life!

በውሃ አቅርቦት፣ በሳኒቴሽንና በሃይጅን ዙሪያ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በውሃ አቅርቦት፣ በፍሳሽ አወጋገድ እንዲሁም በንጽህና አጠባበቅ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር በአዳማ ከተማ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሃገር አቀፍ የምክክር እየተካሄደ ነው።

መድረኩን የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ማዕከል ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ነው።

መድረኩ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ተቋማት ላይ ስለ ውሃ አቅርቦት፣ ፍሳሽ አወጋገድ እና በንጽህና አጠባበቅ ዙሪያ የተካሄደውን የዳሰሳ ጥናት መሰረት በማድረግ፥ ከባለደርሻ አካላት ጋር በመመካከር ለችግሮቹ የጋራ የመፍትሄ አቅጣጫ በማስቀመጥ ወደ ተግባር መግባትን አላማው ያደረገ ነው ተብሏል።

በጤና ሚኒስቴር የሃይጅንና አካባቢ ጤና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ ኢክራም ሬድዋን፥ የጤና ሚኒስቴር በኢንቨስትመንት ተቋማት ላይ ሃይጅንና አካባቢ ጤና አጠባበቅ ላይ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል።

በርካታ የሰራተኛ ቁጥር ባላቸው እነዚህ ተቋማት የተላላፊ በሽታዎች ስርጭት ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው፥ በሽታዎቹ ከውሃ አቅርቦትና ከፍሳሽ አወጋገድ እንዲሁም ከንጽህና አለመሟላት ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ገልጸዋል።

ተቋማቱ እነዚህን ማሟላትና የአካባቢ ንጽህና ላይ ትኩረት ሰጥተው መስራት ስለሚገባቸው በጋራና በቅንጅት ችግሮቹን ለማስወገድ የምክክር መድረኩ መዘጋጀቱንም አንስተዋል።
በምክክር መድረኩ ላይ በ19 የኢንቨስትመንት ተቋማት ላይ የተደረገው የዳሰሳ ጥናት ቀርቧል።

በውሃ አቅርቦት፣ የፍሳሽ አወጋገድ እና በንጽህና አለመሟላት ሳቢያ ተላላፊ በሽታዎች በኢንቨስትመንት ተቋማት በርካታ ሰዎችን እያጠቁ እንደሚገኙ በጥናቱ መገለጹን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.