Fana: At a Speed of Life!

ጭፍራ አካባቢ የተፈናቀሉ ዜጎች ለችግር መጋለጣቸውን ተናገሩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የህወሃት የሽብር ቡድን የከፈተውን ጥቃት ተከትሎ ከአፋር ክልል ጭፍራ አካባቢ የተፈናቀሉ ዜጎች ለችግር መጋለጣቸውን ተናገሩ።

የሽብር ቡድኑ ሰርጎ ለመግባት የከፈተውን ጥቃት ተከትሎ በክልሉ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል።

ህዝብን በጠላትነት የፈረጀው የሽብር ቡድኑ በጭፍራ በንፁሃን ላይ ከባድ መሳሪያ መተኮሱን ተከትሎ ከአካባቢው መፈናቀላቸውን የሚያስረዱት ተፈናቃዮች ÷ አሸባሪ ቡድኑ የአዕምሮ ህሙማንን ጨምሮ ንፁሃንን መግደሉን ነው የገለፁት።

የከፈተውን የሽብር ጥቃት ተከትሎ ልጅና ወላጅ ንብረትና ባለንብረት ተለያይተዋል ፤ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ የህዝብ ተቋማትም ወድመዋል ነው ያሉት።

የሽብር ቡድኑን ጥቃት ሽሽት በርካቶች የተፈናቀሉ ሲሆን ÷ በአፋር ክልል በተቋቋሙ ጊዜያዊ መጠለያዎች መስፈራቸውን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ባደረገው ቅኝት ተመልክቷል።

ተፈናቃዮቹ በሽብር ቡድኑ ጥፋት ከቤታቸው መፈናቀላቸውንና እርዳታ ፈላጊ መሆናቸውን ይናገራሉ።

አሁን ላይም በቂ ድጋፍ እንደማያገኙና እርዳታ እንዲደረግላቸውም ጠይቀዋል።

የዜጎች ሞትና መፈናቀል የሚያበቃው የጁንታው ግብዓተ መሬት ሲፈፀም መሆኑን ጠቅሰው፥ ጦርነቱ በአጭር ጊዜ ተጠናቆ ወደቀደመ ህይወታቸው እስከሚመለሱ በሚችሉት ሁሉ ድጋፋቸውን እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።

በአፈወርቅ እያዩና ፀጋዬ ወንድወሰን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.