Fana: At a Speed of Life!

የመከላከያ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ምረቃና ልዩ የጀግንነት ተግባር ለፈፀሙ የሠራዊቱ አባላት የሽልማትና ዕውቅና ስነስርዓት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ምረቃና ልዩ የጀግንነት ተግባር ለፈፀሙ የሠራዊቱ አባላት የሽልማትና ዕውቅና ስነስርዓት ተካሄደ፡፡

የሚኒስቴሩ ዋና መስሪያ ቤት አዲስ ህንጻ በ13 ሺህ ካሬ ስፋት ላይ ያረፈ ሲሆን፥ ባለ 5 ወለል እና ከ700 በላይ ቢሮዎች ያሉት ህንጻ ነው፡፡

በውስጡም የተለያየ ደረጃ ያላቸው የስብሰባ አዳራሾች፣ ቤተመፃህፍት፣ የምርምር ማዕከላትና የተደራጀ የመረጃ ማዕከልን አካቷል፡፡

በምርቃ ስነስርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ፣ ሚኒስትሮች፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ የመከላከያ ሰራዊት አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው አካላት ተገኝተዋል፡፡

በስነ ስርዓቱ ላይም የተለያዩ ወታደራዊ ትርዒቶች እየቀረቡ ይገኛሉ፡፡

ዋና መስሪያ ቤቱ ጦር ሃይሎች ቀጠና ሁለት በሚገኝ የቀድሞ የአውሮፕላን ማረፊያ ስፍራ ላይ የተገነባ ነው፡፡

የህንጻው ኪነ ህንጻ ከኢትዮጵያውያን ስነ ልቦና እና ፍልስፍና ተቀድቶ የተዘጋጀ ሲሆን ፥ ከላይ ጦር እና ጋሻ ሆኖ ይታያል ፤ ይህም የመከላከያ ሰራዊት ሃገር የመጠበቅ ሚናውን የሚያንጸባርቅ ነው፡፡

የቀድሞው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ሕንጻ አሁን መከላከያው ለሚሠራው ዘመናዊነትን እና ቴክኖሎጂን ያማከለ ሥራ የማይመች በመሆኑ አዲስ ሕንጻ መገንባት በማስፈለጉ ሕንጻው መገንባቱን ነው ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ የገለጹት፡፡

ፊልድ ማርሻሉ የቀድሞው ሕንጻ ቢሮዎች ጠባብ እና ለሥራ ምቾት የማይሰጡ ከመሆናቸውም ባሻገር ዘመኑን የሚመጥኑ ቴክኖሎጂዎችን ያላሟሉ ነበሩም ነው ያሉት፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.