Fana: At a Speed of Life!

ለሪፐብሊኩ ጥበቃ ሃይል የሰራዊት አባላት ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ሰራተኞች፣ የመዲናዋ ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት በህክምና ላይ ለሚገኙ የሪፐብሊኩ ጥበቃ ሃይል የሰራዊት አባላት ድጋፍ አደረጉ፡፡
ድጋፉ ከ70 ሺህ ብር በላይ ግምት ያላቸው የተለያዩ የስፖርት ትጥቆች፣ የምሳ ግብዣ እና የንጽህና መጠበቂያዎችን ያካተተ መሆኑን ከመከላከያ ሰራዊት ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ለሀገር ህልውና እየከፈለ ያለው መስዋዕትነት ከምንጊዜውም በላይ በወርቃማ ብዕር የሚፃፍ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አገልግሎቶችና መልካም አስተዳደር ክትትል ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ አለምፀሀይ ጳውሎስ እና የአዲስ አበባ ወጣቶች ስፖርት ቢሮ ሃላፊ አቶ አብርሃም ታደሰ ተናግረዋል፡፡
እናንተም የሪፐብሊኩ ጥበቃ ሃይል የሰራዊት አባላት ህዝብ እና መንግስት የሰጣችሁን አደራ በጀግንነት እየተወጣችሁ ላበረከታችሁት አስተዋጽኦ እናመሰግናለን ብለዋል፡፡
ለተደረገው ድጋፍ በሰራዊቱ ስም ምስጋና ያቀረቡት ደግሞ÷ የሪፐብሊኩ ጥበቃ ሃይል ምክትል አዛዥ ለሰው ሃብት ጠቅላላ አገልግሎት ሃላፊ ብርጋዴር ጀነራል አብድሮ ከድር ናቸው፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.