Fana: At a Speed of Life!

ለዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር በቂ ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል – ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር በቂ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የ2016 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ የቅድመ ዝግጅት እና ቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች ላይ ብሄራዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ዐቢይ ኮሚቴ የምክክር መድረክ አካሂዷል።

የኮሚቴው አስተባባሪ የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) እንዳብራሩት፤ የመድረኩ ዓላማ የ2016 ዓ.ም የችግኝ ተከላ የቅድመ ዝግጅት ምዕራፍን መገምገም ነው።

በተጨማሪም ቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች ላይ የጋራ መግባባት ላይ መድረስ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

በ2015 ዓ.ም በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር 7 ነጥብ 5 ቢሊየን ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸው ችግኞች መተከላቸውንም አስታውሰው፤ በተደረገው የዳሰሳ ጥናት የተተከሉ ችግኞች የጽድቀት መጠንን 90 ከመቶ ማድረስ እንደተቻለ ገልፀዋል፡፡

ለዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር 6 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል ዕቅድ መያዙን ጠቅሰው፤ ለዚህም 7 ነጥብ 2 ቢሊየን ችግኝ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

በአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ለሚተከሉ ችግኞችም በሀገር አቀፍ ደረጃ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር መሬት ለተከላ መዘጋጀቱንም መግለፃቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.