Fana: At a Speed of Life!

ለቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ የሁሉም ክልሎች የፀጥታና ደህንነት ድክመትና ጥንካሬ መለየቱ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በዘንድሮው 6ኛ ሀገራዊ ምርጫ የፀጥታና ደህንነት ችግር እንዳያጋጥም ከወዲሁ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ።

ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በምርጫው ዕቅድ፣ ሀገራዊ የደህንነት ስጋቶች እንዲሁም የመፍትሄ አቅጣጫዎች ላይ ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ተወያይተዋል።

የምርጫውን ደህንነት ለማስጠበቅ በአገር አቀፍ ደረጃ የተቋቋመው ግብረሃይል ቀደም ሲል ባካሄደው ውይይት ክልሎች የየአካባቢያቸውን ችግሮች ለይተው የፀጥታ ዕቅድ እንዲያወጡ አቅጣጫ አስቀምጧል።

በዚሁ መሰረት ክልሎቹ ያወጡት ዝርዝር ዕቅድ ዛሬ ተገምግሞ ቀጣይ አቅጣጫ ተሰጥቶበታል።

የምርጫውን ደህንነት የሚፈታተኑ ችግሮችን ለይቶ ከፀጥታና ከሕግ አፈፃፀም አኳያ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ ላይ ያተኮረው ውይይት ምርጫውን ሠላማዊ ማድረግ በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ መክሯል።

የምርጫ ዕቅድ ሪፖርት ካቀረቡ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች አዲስ አበባ፣ አማራ፣ ኦሮሚያና ሀረሪ ክልሎች የተሻለ ዕቅድ፣ ይዘትና ነባራዊ ሁኔታን ተንትኖ በማስቀመጥ ተሽለው ተገኝተዋል ተብሏል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው ምርጫው ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲካሄድ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

እያንዳንዱ ክልል ከፀጥታና ደህንነት አኳያ በተገቢው ትኩረት ችግሮችን ለይቶ መስራት አለበት ነው ያሉት።

ከዚህ አንፃር የምርጫውን ተሳታፊ አካላት መሰረት ያደረገ ዝርዝር ዕቅድ መውጣቱን ተናግረዋል።

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በዕቅዱ የሁሉም ክልሎች ድክመትና ጥንካሬ መለየቱንና ዕቅዱ ምን ያህል ተጨባጭና ነባራዊ ሁኔታዎችን አይቷል የሚለው መገምገሙን መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በዕቅዱ መሰረት ክልሎች የምርጫ አፈፃፀሙን ሠላማዊ ማድረግ አለባቸው ያሉት ሰብሳቢዋ ከዚህ አንፃር ክፍተት ያለባቸው ችግሮቹን በቶሎ እንደሚያርሙ ነው የተናገሩት።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.