Fana: At a Speed of Life!

ለአሸባሪው የትህነግ ቡድን አሉባልታ ጆሮ መስጠት አያስፈልግም – የወልዲያ ከተማ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 21፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የወልድያ ከተማ ነዋሪዎች በጦር ግንባር ድል ያልቀናው አሸባሪው የትህነግ ቡድን ለሚያሰራጨው አሉባልታ ጆሮ መስጠት እንደማያስፈልግ ገለጹ፡፡
የከተማው ነዋሪዎች የአሸባሪው ቡድን አባላት ሐሰተኛ መረጃዎችን በማኅበራዊ ትስስር ገጾች እያስተላለፉ ቢሆንም ችላ ብለን የተጋረጠብንን የህልውና አደጋ ከሠራዊቱ ጋር በጋራ መመከት ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡ በሌላ በኩል የሰሜን ዕዝ ኢንዶክትሬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ ሌተናል ኮሎኔል ሌችሳ መገርሳ እንደጠቆሙት÷ በግንባር የሚገኘው ሠራዊት ግዳጁን እንዲወጣ የሰሜን ወሎ ሕዝብ የሚጠበቅበትን እያደረገ በመሆኑም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
አያይዘውም ጠላት በሚያሰራጨው የሐሰት ፕሮፓጋንዳ ሕዝቡ ሳይደናገር ሁሉም ወታደር ሆኖ የህልውና ዘመቻውን ከዳር እንዲያደርስ ጥሪ ማቅረባቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.