Fana: At a Speed of Life!

ልጁን የሂሳብ ትምህርት በማስጠናት ለልብ ድካም የተዳረገው ግለሰብ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 28 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አንድ ቻይናዊ አባት ልጁን የሂሳብ ትምህርት በማስጠናት ለልብ ድካም መዳረጉ ተሰምቷል፡፡

ይህ ግለሰብ የሶስት ዓመት ወንድ ልጁን በሃገሪቱ ትምህርት ከተጀመረበት ቀን ጀምሮ የሂሳብ ትምህርት በማስጠናት ላይ ነበር ተብሏል፡፡

ነገር ግን የ45 ዓመቱ ቻይናዊ ላለፉት ሁለት ሳምንታት ትምህርቱን ሲያስጠና በተበሳጨ ቁጥር በደረቱ ላይ ትንሽ ህመም ይሰማው ነበር ነው የተባለው፡፡

ሁኔታው እየበሳ ስለመጣም ወደ ሆስቲታል መወሰዱ ተገልጿል፡፡

በዛም ቻይናዊው አባትም ዋና የደም ቧንቧው አንድ ክፍል እንደተዘጋ የታወቀ ሲሆን ይህ የደም ቧንቧ መዘጋት የልብ የደም አቅርቦትን እያቋረጠ ነበር ተብሏል፡፡

ሐኪሞች እንዳሉትም ለብዙ ዓመታት ሲጋራ ማጨሱ ለታካሚው ለልብ ድካም መጋለጥ አስተዋፅኦ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ባለፈ ግን ልጁን ሲያስረዳ ከፍተኛ ጭንቀትና ቁጣ ነበር ብለዋል፡፡

ግለሰቡ በቶሎ ወደ ሆስፒታል ባይመጣ ጉዳቱ ከዚህ የከፋ ይሆን እንደነበርም አስረድተዋል፡፡

አሁን ላይ ቻይናዊው አባትቀዶ ጥገና የተደረገለት ሲሆን በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኝም ኦዲቲ ሴንትራል አስነብቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.