Fana: At a Speed of Life!

መገናኛ ብዙሃን የኢትዮጵያን እንደ አገር መቀጠል ማዕከል ባደረገ መልኩ ሊሰሩ ይገባል – ምሁራን

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች እና ተቋማት አሁን አገር ከገባችበት ችግር አንጻር የጋዜጠኝነትን መርሆዎች ባከበረ እና የኢትዮጵያን እንደ አገር መቀጠል ማዕከል ባደረገ መልኩ ሊሰሩ እንደሚገባ ምሁራን ገለጹ።
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ጋዜጠኝነት እና ኮሙኒኬሽን መምህሩ ዶክተር አደም ጫኔ እንዳሉት፥ አገር የአንድ ፓርቲ እና ተቋም ጉዳይ ብቻ ሳትሆን በሁሉም ዜጎቿ ጥረት እና ዋጋ የምትጸና ናት።
ከዚህ አንጻርም መገናኛ ብዙሃን ስለሚተላለፉ መረጃዎች ጥቅም እና ጉዳት በመረዳት የአገርን ጥቅም ባስቀደመ መልኩ ሊሰሩ ይገባል ነው ያሉት።
የጂማ ዩኒቨርሲቲ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን መምህሩ ዶክተር ደመላሽ መንግስቱ በበኩላቸው፥ በሚዲያ ተቋማት እና ማህበራዊ ሚዲያ የህልውና ዘመቻውን ከግምት ያላስገባ የመረጃ አጠቃቀም እንደሚስተዋል ይገልጻሉ።
እንደ እርሳቸው ገለጻ የተለያዩ ወታደራዊ መረጃዎች እና የደህንነት ጉዳዮች በምስጢር ሊያዙ ሲገባቸው በቀላሉ ሲሰራጩ ይስተዋላል።
በአገር እና በዜጎች ጉዳይ ገለልተኛ ነኝ ተብሎ የሚታለፍበት ሊሆን አይገባም የሚሉት ምሁራኑ መሰል ድርጊት በሚፈጽሙት ላይ መንግስት እርምጃ ሊወስድ ይገባል ብለዋል።
በእንዲህ አይነት የቀውስ ወቅትም ቀውሱን የተመለከቱ መረጃዎች ከአንድ ማዕከል ለመገናኛ ብዙሃን እና ተደራሲያን መድረስ እንደሚጠበቅበትም ገልጸዋል።
በአፈወርቅ አለሙ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.