Fana: At a Speed of Life!

ሲቪክ ማህበራት ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የራሳቸውን ሚና መጫወት  እንደሚገባቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ማቶ ማሩ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሲቪክ ማህበራትየራሳቸውን ሚና መጫወት  ይገባቸዋል ሲሉ ገለጹ።

ከለውጡ በኋላ ከተሰራው ስራዎች ውስጥ አንዱ የሲቪክ ማህበራት ሚናቸውን ከፍ እንዲያጉ ለማድረግ በርካታ ስራዎች መከናወኑን አንስተዋል።

የማህበራቱን ሚና ከማሳደግ ባለፈ አሳሪ ህጎችን የመፍታትና ተቋማትን ለመገንባት የተከናወኑ ተግባራቶች በተሻለ መልኩ ሊገለፅ የሚችል መሆኑንም ተናግረዋል።

የሲቪክ ማህበራት ለዲሞክራሲ ስርዓትና ለሀገር ግንባታ የሚኖረው ሚና ከፍተኛ መሆኑን በማንሳት በዚህ ወቅት ከቀደሙት ጊዜያቶች በተሻለ መልኩ ምቹ ሁኔታ መኖሩ ይታወቃል ብለዋል

በምርጫው ወቅትም የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ  ጠቅላይ አቃቤ ህጉ ጠይቀዋል።

ከዚህ ቀደም ሀገር በቀል የሆኑ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተሳትፎና ሚና አነስተኛ እንደነበረ የገለፁት ደግሞ አቶ መሱድ ገበየው የኢትዮጵያ የሰባዊ መብቶች ድርጀቶች ህብረት ዳይሬክተር ናቸው።

አዲሱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ከተሻሻለ በኋላ ባለፋት ሁለት አመታት የተሻለ የመነቃቃት ስሜት ቢፈጠርም የአቅም ማነስ ችግር መኖሩንና የአቅም ግንባታ መሰል ስራዎችን በመሰራት ለማጎልበት ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ ገልጸው÷በቀጣይም ተጠናክሮ እንዲሚቀጥሉ  ተናግረዋል ።

በዛሬው እለትም በደቡብና በሲዳማ ክልሎች ለሚንቀሳቀሱ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶችበሰብዓዊ መብትና ምርጫ ላይ ያተኮረ ስልጠና በሀዋሳ ከተማ  እየተሰጣቸው ይገኛል።

በብርሃኑ በጋሻው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.