Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) በኮሪደር ልማት ሥራ ላይ ከአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር አመራሮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ሥራን በተመለከተ ከከተማ አሥተዳደሩ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

ከአንድ ወር በፊት የኮሪደር ልማት ሥራ ሂደት ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አጠቃላይ ግምገማ መደረጉን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ “ዛሬ እንደገና ከአዲስ አበባ አሥተዳደር አመራሮች እና የኮሪደር ልማት ሥራ መሪዎች ጋር በመገናኘት በሥራዎቻችን ርምጃ ዙሪያ ጥልቀት ያለው ውይይት አድርገናል” ሲሉ ገልጸዋል፡፡

እነዚህን ሥራዎቻችን የግንባታ ጉዳዮች ብቻ አይደሉም፤ ይልቁንም ከተማችንን ወደ ላቀ ምቹ፣ ንቁ እና ዘላቂ የመኖሪያ ከባቢ የመለወጥ ጥረቶች ናቸው ሲሉም ነው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው የገለጹት፡፡

ሥነ-ውበትን በማሳደግ፣ አረንጓዴነትን በማስፋት ብሎም መሰረተ-ልማትን በማሻሻል የሕዝባችንን ጤና ከመጠበቅ ባሻገር የሥራ ዕድሎችንም እየፈጠርን ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

እነዚህ የጋራ ጥረቶቻችን የአዲስአበባን አጠቃላይ ይዞታ በማላቅ እውነትም ለሁሉም ነዋሪዎቿ ፍላጎቶች የተመቸች ያደርጓታል ነው ያሉት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.