Fana: At a Speed of Life!

የማር የጤና በረከቶች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ማር ከዕፅዋት አበባ በማር ንቦች የሚሰራ ፈሳሽ ውህድ ሲሆን በንጥረ-ምግቦች እና አንቲኦክሲዳንትስ የበለፀገ ፥ ፀረ-ባክቴሪያ ባህሪይ አለው፡፡

ማር በርካታ የጤና ጥቅሞች ያሉት ሲሆን ፥ በቤት ውስጥ ለሚደረግ የህክምና እና የምግብ አማራጭ ሆኖ ያገለግላል፡፡

ማር ፕሮቲን፣ ፋይበር እንዲሁም በውስጡ አነስተኛ መጠን ያላቸው ንጥረ ነገሮችን የያዘ በመሆኑ ለጤና የሚሰጠው ጠቀሜታ ከፍ ያለ ነው፡፡

ማር ምንም እንኳን ልክ እንደሌሎች የስኳር ዓይነቶች በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ከፍ የሚያደርግ ቢሆንም በውስጡ የያዘው ፀረ-አንቲኦክሲዳንትስ ከሜታቦሊክ ሲንድረም እና ከዓይነት 2 የስኳር በሽታ ይከላከላል፡፡

ማር የልብ ጤንነትን እንደሚጠብቅ እና ደም ግፊትን ለመቀነስ፣ በደም ውስጥ የሚገኝን የቅባት መጠን ለማሻሻል፣ የልብ ምትን ለማስተካከል እና ጤናማ ሴሎች እንዳይሞቱ እንደሚረዳም ጥናቶች ያስረዳሉ፡፡

በተጨማሪም ማር የኮሌስትሮል መጠንን ለማስተካከል እንደሚረዳ ተገልጿል፡፡

ማር ፀረ-ባክቴሪያ በመሆኑ የቃጠሎ አደጋን እና ቁስልን እንዲሁም የቆዳ ላይ ችግሮች ለማከም ፍቱን እንደሆነ ይነገራል፡፡

ከአንድ ዓመት በላይ ለሆኑ ህጻናት ማር እንደ ተፈጥሯዊ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ሳል መከላከያ መጠቀም የሚመከር እንደሆነም ይነገራል፡፡

እንዲሁም ከ 1 አመት በታች የሆኑ ህጻናት ማር መብላት እንደሌለባቸው እና አዋቂ ሰዎችም ቢሆኑ ማርን በሚመገቡበት ጊዜ መጠኑ ላይ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚኖርባቸው የኸልዝላይን መረጃ አመላክቷል፡፡

በተጨማሪም የጤና ችግር ያለበት ሰውማር ከመውሰዱ በፊት ሃኪም ማማከር እንደሚገባ መረጃው አስታውሷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.