Fana: At a Speed of Life!

ሴቶች ከወንዶች ይልቅ የደም ግፊት መጠናቸው ከፍ ያለ መሆኑን አንድ ጥናት አመላከተ

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሴቶች ከወንዶች ይልቅ ለከፍተኛ ለደም ግፊት ተጋላጭ መሆናቸውን ጥናት አመለከተ።

ከዚህ ቀደም የተደረጉ ጥናቶች ወንዶች ከሴቶች ይልቅ ለደም ግፊት በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ መሆናቸውን ያመላክታሉ።

በአሜሪካ የተደረገና ከሰሞኑ ይፋ የሆነ አንድ ጥናት ግን የደም ግፊት መጠን ከወንዶች ይልቅ በሴቶች ላይ እንደሚጨምር አመላክቷል።

ጥናቱ ዕድሜያቸው ከ5 እስከ 98 ዓመት በሆናቸው 32 ሺህ 833 ሰዎች የተካሄደ ሲሆን፥ ከእነዚህ ውስጥ 17 ሺህ 733ቱ ሴቶች ናቸው።

በጥናቱ ውጤት መሰረት በ20ዎቹ እድሜ ክልል ላይ ወንዶች ከፍ ያለ የደም ግፊት ይስተዋልባቸዋል ነው ያሉት።

ይሁን እንጅ ሴቶች በ40ዎቹ እድሜያቸው ከፍ ያለ የላይኛው (ሲነበብ) የደም ግፊት አለባቸውም ነው ያሉት አጥኝዎቹ።

የታችኛው (ሲነበብ) የደም ግፊት ግን በሁለቱም ጾታዎች ተመሳሳይ ሆኖ ተገኝቷልም ብለዋል።

በአጠቃላይ ግን ሴቶች ከወንዶች ይልቅ ከፍ ያለ የደም ግፊት እንደሚስተዋልባቸው በጥናት ውጤታቸው ገልጸዋል።

በጥናቱ ሴቶች ከልጅነት ጀምሮ የደም ግፊት መጠናቸው ከፍተኛ ከሆነ በኋለኛው የእድሜ ዘመናቸው ለልብና ለደም ቧምቧ በሽታ ተጋላጭ እንደሚሆኑም አስረድተዋል።

ምንጭ፦ upi.com/

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.