Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን በአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ የቡሩንዲ አቻውን አሸነፈ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 9፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን በአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታየቡሩንዲ አቻውን አሸነፈ፡፡ በኮስታሪካ እና ፓናማ አዘጋጅነት ለሚካሄደው 10ኛው የሴቶች ከ20 አመት በታች አለም ዋንጫ ለማለፍ የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች የሴቶች ብሄራዊ ቡድን የማጣሪያ ጨዋታውን ዛሬ ቡጁምብራ ላይ ከቡሩንዲ ጋር አድርጎ 5 ለ 0 አሸንፏል፡፡ 16 ሀገራትን በሚያሳትፈው የአለም ዋንጫ ላይ አፍሪካን ወክለው ከሚሳተፉት 2 ሀገራት መካከል አንዱ ለመሆን ነው ማጣሪያውን እያደረጉ የሚገኙት
Read More...

ቀነኒሳ በቀለ በለንደን ማራቶን ከኪፕቾጌ ጋር ይፎካከራል

አዲስ አበባ ፣ ጥር 8 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ቀነኒሳ በቀለ ሚያዚያ ወር ላይ በሚካሄደው የለንደን ማራቶን ከኬንያዊው ኤሉድ ኪፕቾጌ ጋር እንደሚሮጥ አስታወቀ። ቀነኒሳ ከኪፕቾጌ ጋር ዳግም ለመወዳደር ዝግጁ መሆኑን ገልጿል። ውድድሩን አስመልክቶ በሰጠው አስተያየትም በውድድሩ የተሻለ ነገር ለማድረግ ጥሩ መስራ መስራቱንም ነው የተናገረው። ጉዳት ባለፉት አመታት…

የ2021 የአፍሪካ ዋንጫ ጥር ወር ላይ እንደሚካሄድ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2021 የአፍሪካ ዋንጫ ጥር ወር ላይ እንደሚካሄድ አስተናጋጇ ካሜሮን ገለፀች። ትናንት የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) እና የካሜሮን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያካሄዱትን ስብሰባ ተከትሎ የካፍ ፕሬዚዳንት የአፍሪካ ዋንጫ ከፈረንጆፐቹ ጥር 1 እስከ 29 ድረስ እንደሚካሄድ በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል። የአፍሪካ ዋንጫ…

ወላይታ ድቻ የቀድሞ አሰልጣኙ ወደ ስራ እንዲመለሱ ጥሪ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ጥር 7፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የወላይታ ድቻ እግር ኳስ ክለብ የቀድሞ አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ ወደ ስራ እንዲመለሱ ጥሪ አቀረበ። ክለቡ አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ በ8ኛ ሳምንት በሜዳቸው ላይ መሸነፋቸውን ተከትሎ በስራ ገበታቸው ላይ ያልተገኙበትን ማስረጃ በመያዝ ወደ ምድብ ስራቸው እንዲመለሱ ጥሪ ማቅረቡን አስታውቋል። ክለቡ በቀጣይ ከጅማ አባጅፋር…

ባርሴሎና አሰልጣኝ ኤርኔስቶ ቫልቬርዴን በማሰናበት ኪኬ ሴቲዬን አዲሱ አሰልጣኝ አድርጎ ሾሟል

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የስፔኑ ሀያል የእግር ኳስ ክለብ ባርሴሎና አሰልጣኝ ኤርኔስቶ ቫልቬርዴን በማሰናበት ኪኬ ሴቲዬን አዲሱ አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙ ተሰምቷል። የ55 ዓመቱ አሰልጣኝ ኤርኔስቶ ቫልቬርዴ ባርሴሎናን በመሩበት ጊዜ ክለቡ ሁለት የስፔን ላሊጋ ዋንጫዎችን እንዲያነሳ እና የዘንድሮውን የላሊጋ ውድድር በግብ ልዩነት እንዲመራ አድርገዋል።…

በኔዘርላንድስ ግማሽ ማራቶን አትሌት ፀሃይ ገመቹ አሸናፊ ሆናለች

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኔዘርላንድስ በተካሄደ የሴቶች ግማሽ ማራቶን ሩጫ ውድድር አትሌት ፀሃይ ገመቹ አሸናፊ ሆናለች። አትሌት ፀሃይ ርቀቱን 1 ሰዓት ከ20 ደቂቃ ከ29 ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት ስታሸንፍ፥ አትሌት ታደለች በቀለ ሶስተኛ በመሆን አጠናቃለች። በተመሳሳይ በስፔኑ ሁዋን ሙጉዬርዛ አመታዊ የግማሽ ማራቶ ውድድር አትሌት ታደሰ ወርቁ…

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 8ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በተለያዩ ከተሞች ተካሂደዋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 03፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 8ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በዛሬው ዕለት በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች ተካሂደዋል። በዚህም ወልቂጤ ከተማን ከሜዳው ውጭ የገጠመው የአምናው ሻምፕዮን መቀሌ 70 እንደርታ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የሊጉን መሪነት ተረክቧል በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ቡናን በሜዳው ያስተናገደው ፋሲል ከነማ 2ለ1 በሆነ ውጤት…